image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የ2 ት/ቤቶች የማስፋፊያ ግንባታ ስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት መርሀ ግብር አከናወነ ።

ታህሳስ 22, 2018
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የ2 ት/ቤቶች የማስፋፊያ ግንባታ ስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት መርሀ ግብር አከናወነ ። በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ሰራውን ያስጀመሩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የት/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት እንደገለጹት ለትውልድ እና ለሀገር ግንባታ ቅድሚያ በመስጠት ይን የማስፋፊያ ግንባታ ለሳጀመረው ለክፍለ ከተማው አስተዳደር ምስጋናቸውን በማቅረብ ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። በመቀጠልም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልእልቲ እንደገለጹት ዛሬ ያስጀመርነው የማስፋፊያ ግንባታ በመምህራን እና በወላጆች ዘንድ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደነበርና የግንባታ ስራን እንዳስጀመርን ሁሉ በቅርብ ጊያት ውስጥ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አጠናቀን ለአገልግሎት እንደሚበቃ ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች