image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የፅ/ቤቶች እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ።

መጋቢት 14, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ9 ወር ታቅደው የተከናወኑ የፅ/ቤቶች አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ስራዎች ላይ ተወያይቷል። በመድረኩ ላይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነ ደረሰን ጨምሮ የክ/ከተማ ሴክተር ፅ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባለፉት 9 ወራት የተሰራው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው በጋራ የመስራት ባህላችንን በማሳደግ የነዋሪዎቻችንን ጥያቄዎች ማርካት መቻል አለብን ብለዋል በተጨማሪም ተቋማት ተግባራትን በቅንጅታዊ አሰራር በመምራት በቀሪዎቹ ጥቂት ወራቶች እቅዶቻችንን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በ2017 በጀት አመት በ9 ወራት ታቅደው የተከናወኑ መደበኛ እና ወቅታዊ ስራዎችን የነበራቸው ውጤታማ አፈፃፀም የተሻለ እንደነበር ገልፀው ቀሪ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ አስገንዝበዋል። ባለፉት 9 ወራት በስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ለ18,709 ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን 584 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ለ 60 ኢንተርፕራዞች 51,000,000 ብር ብድር ማመቻቸትም የተቻለ ሲሆን 10,014 ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር በመፍጠር 484,000,000 ገቢ እንድያገኙ ተደርጋል፡፡ አስተዳደሩ በ9 ወር ውስጥ በልደታ ክ/ከተማ በገቢ ቅርጫፍ ፅ/ቤት 2,348,089,000 ብር 102.19 ፐርሰንት ብር ከገቢ ሰብሳቢ ተቋማት መሰብሰብ የቻለ ሲሆን የልደታ ክ/ከተማ ፈይናንስ ፅ/ቤት 1,016,000 ብር በኦዲት ተመላሽ ማድረግ መቻሉን ተገልፆል፡፡ ከዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች አንፃር በመንግስት የተሰሩ 15 ፕሮጀክቶች ክትትል በማድረግ 8 ግንባታቸውን ያጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ርክክብ ያከናወነ ሲሆን በቤቶች አስተዳደር 87,104,540 ሚሊዮን የሚጠጋ ገቢ ከኪራይ ና ከንግድ ኪራይ መሰብሰብ መቻሉን እና በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 228 የመንግስት ቤቶች በህግ በማስወሰን ለልማት ተነሺና ለደሀ ደሀ አካላት ርክክብ ተደርጋል፡፡ ጤናን በተመለከተ የመሰረታዊ መድሃኒት ስርጭት 95 በመቶ እንዲሁም የህይወት አድን መድሃኒት አቅርቦት 92 በመቶ ማድረስ የተቻለ ሲሆን በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ለ 90,008 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የማእድ ማጋራት ስራ እና የ" 571" አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት በማከናወን ከ አንድ ቢሊዬን ብር በላይ ለተለያዩ የመሰረታዊ ልማት ስራዎች በበጎ ፍቃደኞች መሰብሰብ መቻሉንም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል፡፡ ከወጣቶች እና ስፖርት ስራዎች አንፃር ለ 209,857 ወጣቶች በተለያዩ ርእሰ ጉዳዬች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ለ 10,247 ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ከፍትህ ስራዎችን በተመለከተ ባለፉት 9 ወራት 214 መዝገቦች የተንቀሳቀሱ ሲሆን በ108 መዝገቦች ውሳኔ አግኝተዋል።ውሳኔ ካገኙት 108 መዝገብ ውስጥ" 102 "ለመንግስት ተወስነዋል። ውሳኔ ካገኙት መዝገቦች 39,941,710 ብር የሚገመት የመንግስት ሀብት ማዳን ተችሏል። የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲሁም ቅሬታዎችን በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት "145" የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በክ/ከተማ እና ወረዳ መፍታት መቻሉም በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የምርት አቅርቦት ማሳደግ፣የከተማ ግብርና ስራዎችን ውጤታማ ማድረግ የሪፎርም ስራዎች፣የከተማ ፅዳት እና ማሳዋብ ስራዎች፤በማህበራዊ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰብ ያሉበት ደረጃ በልደታ ክ/ከተማ ፕላንና ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ክብረት አሳምነው ሪፖርት ቀርባል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች