image
image
image
image
image

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡

ግንቦት 4, 2018
የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ የግንቦት 4ቀን 2017 ዓ.ም የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ከመደበኛ ስራ በፊት የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር ተካሄደ። የእለቱ መርኃ-ግብር በጽ/ቤቱ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን ፈጻሚ የሆኑት አቶ ላቀ የኔነህ አቅራቢነት ለአመራሮች እና ሰራተኞች ቀርቦ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡ አቶ ላቀ በአብዛኛው ሰው ዘንድ ብዙም በማይታወቁ በአውቶ ካድ አጠቃቀም ዙሪያ ለአመራሮች እና ለሰራተኞች አቅርበው እውቀታቸውን አሸጋግረዋል፡፡  ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። 

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች