ዜና | Oduu | News
የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል ዘወትር ሰኞ ማልዳ የሚካሄደው የዕውቀት ሽግግር መርኃ-ግብር ተካሂዷል።

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል ዘወትር ሰኞ ማልዳ የሚካሄደው የዕውቀት ሽግግር መርኃ-ግብር ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩም ሰዓቱን ጠብቆ በአቶ አንሙት የቀረበ ሲሆን ሀገራዊ ተረቶቻችንና አስተምህሮዎቻቸው ዙሪያ ያደረገ ሲሆን። አቅራቢው በማብራሪያቸው አለቃ ገብረ ሀናን አብነት አድርገው በአርእስቱ ዙርያ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። ህዳር 15/2018 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ከሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ ግንባታ የዲዛይን ትችት አደረገ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ለሚያስገነባው የወረዳ 5 ጤና ጣቢያ የዲዛይን ትችት ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች በተገኙበት በገነነ ሰለሞን አማካሪ ድርጅት አቅራቢነት ተደረገ። በዲዛይን ትችት መርሀ ግብሩም ላይም በርካታ ግብአቶችን ማግኘታቸውን እና የነበረውን ተሳትፎ በማድነቅ የእለቱ የዲዛይን ትችት መርሀ ግብር መጠናቀቁን የቡድኑ መሪዋ ወ/ት ኮኮቤ ተክለ ማርያም ገልጸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሂደ።

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ። የዕለቱ መርሀ ግብር በምህንድስና ግዢ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አሸናፊ አቅራቢነት የተመራ ሲሆን በኮሚኒኬሽን ምንነትና ጠቀሜታ ዙሪያ በማተኮር ተሞክሯቸውን ለተሳታፊዎች አካፍለዋል። በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። ህዳር 01/2018 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱን የ1ኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈጻጸም ገመገመ።

በልደታ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የ2018 በጀት የ1ኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈጻጸም ከምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከባለ ደርሻ አካላት ጋርና ከሲቪክ ማህበራት ጋር በጋራ ገመገመ። በእቅድ አፈጻጸም የተገኘውን ውጤት በማስቀጠልና በአፈጻጸሙ የተንጠባጠቡ ተግባራት ካሉ በጋራ ሆነን ለአፈጻጸሙ መትጋት እንደሚጠበቅ በመተማመን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫም በጽ/ቤት ኃላፊው በኢንጂነር ቢንያም ሰይፉ ከተቀመጠ በኋላ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዕለተ ሰኞ የአመራርና ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

የዕለተ ሰኞ የአመራርና ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ የእለተ ሰኞ ማለዳ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሐ ግብረ ተካሂዷል። የዕለቱ መርሐ ግብር የተመራው በጽ/ቤቱ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን መሪ በሆኑት በወ/ት በኮከቤ ተ/ማርያም ሲሆን ትኩረቱንም በአዎንታዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ያደረገ ሆኖ በርካታ ልምዶችና ተሞክሮዎች ተንሸራሽረውበታል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አከናውነው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል።  ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የእለተ ሰኞ ማለዳ መስከረም 19/2018 ዓ.ም የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ሰአቱን ጠብቆ ተካሂዷል።

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ የእለተ ሰኞ ማለዳ መስከረም 19/2018 ዓ.ም በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል የሚካሄደው የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ሰአቱን ጠብቆ ተካሂዷል። ስትረስ ማኔጅመንት በሚል ርዕስ የዕውቀት ሽግግር የተደረገ ሲሆን በቢሮው ባልደረባ አቶ ዮሴፍ ሽመልስ አቅራቢነት የዕውቀት ሽግግሩ ተመርቷል። አቅራቢው በመድረኩ እንደገለፁት ስትረስን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል እና ከስትረስ በነጻ መልኩ ስራን በነጻ መልኩ መከወን እንደሚቻል ገለጻ ካደረጉ በኋላና ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ መንፈስ የአገልግሎት ሰጪነት እና የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአባይ ግድብ ግንባታን ስራ መጠናቀቅ አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ተላለፈ።

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም ሰይፉ የአባይ ግድብ ግንባታን ስራ መጠናቀቅ አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላለፉ ። የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ፈጻሚና አመራሮች በተገኙበት መድረክ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ስራ መጠናቀቅና ምርቃትን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የግድቡ ከጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ የግንባታው መጠናቀቅ እስከ ተበሰረበት ያለውን ሂደት ካስቃኙ በኋላ እኛ ኢትዮጽያዊያን ጀምረን የማንጨርሰው ነገር እንደሌለ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በዚህ ፕሮጀክት እውን መሆን ሳንዘናጋ ለሌላ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የነሀሴ 5 ቀን 2017 ዓ/ም የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ።

የነሀሴ 5 ቀን 2017 ዓ/ም የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ። በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ዘወትር የሰኞ ማለዳ የልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር መድረክ የጽ/ቤቱ አመራርና ፈጻሚዎች በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኦዲት ቡድን መሪ በኢንጂነር መንገሻ ቢሰጥ አቅራቢነት የተከናወነ ሲሆን ስለ ኮንቴክስትራ ቀለም ቅብ ምንነትና ጠቀሜታ በሚል እውቀትን በመጋራት በተነቃቃ መንፈስ ወደ ስራ ተገብቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
መደበኛው የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ ።

መደበኛው የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ ። የሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ።/ም የወርቃማው ሰኞ የእውቀት ሽግግርና እና የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር ተከናወነ በእለቱ በ2017 በጀት ዓመት በመድረኩ የመጣ ለውጥና የተገኘ ውጤትን አስመልክቶ ለመወያያ የሚሆን ገላጭና አጠር ያለ ሰነድ ከቀረበ በኋላ በሰነዱ ላይ ለተሰጡ ሀሳብ አስተያየቶች ማብራሪያና የቀጣይ የመድረክ የስራ አቅጣጫ ከጽ/ቤት ኃላፊው ከአቶ ናርዶስ መንክር ከተሰጠ በኋላ በተነቃቃ መንፈስ ወደ ስራ ተገብቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የጀነራል ጃገማ ኬሎ ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ስራው ተጠናቆ የህንጻ ምርቃት ስነ ስርአት ተከናወነ።

የጀነራል ጃገማ ኬሎ ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ስራው ተጠናቆ የህንጻ ምርቃት ስነ ስርአት ተከናወነ። "ትኩረታችን ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ በመገንባት የከተማችንን ብልፅግና ማረጋገጥ ነው" ወ/ሮ አበባ እሸቴ በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከተገነቡ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉ በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባስተላለፍት መልዕክት ዛሬ የተመረቁ የጤና ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ ጤናማ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና አምራች ዜጋ ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ለመሆኑን ምስክር ናቸው ብለው የተመረቁት ጤና ጣቢያዎች ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆኑ የሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከተማ አስተዳደሩ ከ4 ቢሊየን በላይ ወጭ በማውጣት በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብዓትና በባለሙያዎች እንዲደራጁ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል። ዛሬ የተመረቁት የጤና ፕሮጀክቶች ለነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ናቸውም ብለዋል። ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ላደረገው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ምስጋና አቅርበዋል። ዜናው የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ት ነው።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የግንባታ አማካሪዎች የጨረታ ሳጥን ተጫራጮችና ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ተከፈተ።

የግንባታ አማካሪዎች የጨረታ ሳጥን ተጫራጮችና ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ተከፈተ። በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያስገነባቸው ግንባታዎች በሐምሌ 1ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ዘመን ባወጣው ግልጽ ጨረታ የተሳተፉ የአማካሪ ድርጅቶች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተከፍቶ መዋሉን የጨረታ ኮሚቴ አባላት ተናገሩ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት መደበኛ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ።

በልደታ ክ/ከ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት መደበኛ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ። የጽ/ቤቱ አመራርና ፈጻሚዎች በተገኙበት የአንድ አቅራቢን ግዢን በተመለከተ በመንግሥት ግዢ ቡድን ባለሙያ በሆኑት በኢንጂነር አበጀ አቅራቢነትና በጥያቄና መልስ አስተማሪ በሆነ መልኩ ከተከናወነ በኋላ በተነቃቃ መንፈስ ወደ መደበኛ ስራ ተገብቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት መደበኛ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ።

በልደታ ክ/ከ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት መደበኛ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ። የጽ/ቤቱ አመራርና ፈጻሚዎች በተገኙበት የአንድ አቅራቢን ግዢን በተመለከተ በመንግሥት ግዢ ቡድን ባለሙያ በሆኑት በኢንጂነር አበጀ አቅራቢነትና በጥያቄና መልስ አስተማሪ በሆነ መልኩ ከተከናወነ በኋላ በተነቃቃ መንፈስ ወደ መደበኛ ስራ ተገብቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ አበረታች መሆኑ በመስክ ምልከታ ወቅት ተገለጸ

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዲዛይና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመገንባት ላይ የሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ ተደረገ በምልከታውም የስፖርት ማዘውተሪያ ፤ ጤና ጣቢያ ፤ ትምህርት ቤት እና የአስተዳር ህንጻዎች ግንባታ እና የእድሳት ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን እየታየ ያለው የስራ አፈጻጸም ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እና ከዚያም ቀደም ባለ ጊዜ ውስጥ ጥራታቸውን ጠብቀው ሊጠናቀቁ እንደሚችሉ አመላካች ነገሮች በመታየታቸው በአጠቃለይ አሁን ላይ ያላቸው አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ ፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የተክለ ሀይማኖት ጤና ጣቢያ የህንጻ ግንባታ ማስፋፊያ ሥራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

የተክለ ሀይማኖት ጤና ጣቢያ የህንጻ ግንባታ ማስፋፊያ ሥራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ። በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በመከናወን ላይ ከሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንደኛው የሆነው የተክለ ሀይማኖት ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ስራ በጥሩ ጅማሮ ላይ መሆኑ ተገለጸ ። ፕሮጀክቱ መጀመር ከነበረበት ጊዜ በእጅጉን ዘግይቶ የተጀመረ ቢሆንም 7/24 በመስራት በውለታው በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንደሚበቃ በመግለጽ ፕሮጀክቱን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የሚታየውን የህክምና ክፍል እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዕለተ ሰኞ የሰኔ 2 ቀን 2017ዓ/ም የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መረኃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መረኃ-ግብር ተካሄደ፡፡ የእለተ ሰኞ ማለዳ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር ተካሂዷል። የእለቱ መርኃ-ግብር በኢትዮ ኮዲንግ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት በሰው ሀብት አስተዳደር ፈጻሚ በሆኑት በአቶ ቢንያም አቅራቢነት ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። ሰኔ 2/2017 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዕለተ ሰኞ የሰኔ 2 ቀን 2017ዓ/ም የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መረኃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መረኃ-ግብር ተካሄደ፡፡ የእለተ ሰኞ ማለዳ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር ተካሂዷል። የእለቱ መርኃ-ግብር በኢትዮ ኮዲንግ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት በሰው ሀብት አስተዳደር ፈጻሚ በሆኑት በአቶ ቢንያም አቅራቢነት ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። ሰኔ 2/2017 ዓ.ም

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ። በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የሚገኙ የጽ/ቤቱ አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝታቸውም በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአይነትም በጥራትም በአፈጻጸም ብቃትም ቀድሞ የነበረንን የስራ ባህል ተቀይሮ ያየንበትና በጥብቅ የአመራር ዲሲፕሊን እየተመራ መሆኑን ገለጹ። በመቀጠልም የፕሮጀክቶች በጊዜ መጠናቀቅ የተገልጋዩን ህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን መልስ ይሰጣሉ ብለዋል ። በመጨረሻም የፕሮጀክቶች በጊዜ መጠናቀቅ ለቀጣይ በጀት አመት ስንቅ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ። በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የሚገኙ የጽ/ቤቱ አመራርና ፈጻሚዎች በግንባታ ስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶን የመስክ ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝታቸውም በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአይነትም በጥራትም በአፈጻጸም ብቃትም ቀድሞ የነበረንን የስራ ባህል ተቀይሮ ያየንበትና በጥብቅ የአመራር ዲሲፕሊን እየተመራ መሆኑን ገለጹ። በመቀጠልም የፕሮጀክቶች በጊዜ መጠናቀቅ የተገልጋዩን ህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን መልስ ይሰጣሉ ብለዋል ። በመጨረሻም የፕሮጀክቶች በጊዜ መጠናቀቅ ለቀጣይ በጀት አመት ስንቅ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡

የዕለተ ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር ተካሄደ፡፡ የግንቦት 4ቀን 2017 ዓ.ም የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ከመደበኛ ስራ በፊት የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር ተካሄደ። የእለቱ መርኃ-ግብር በጽ/ቤቱ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን ፈጻሚ የሆኑት አቶ ላቀ የኔነህ አቅራቢነት ለአመራሮች እና ሰራተኞች ቀርቦ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡ አቶ ላቀ በአብዛኛው ሰው ዘንድ ብዙም በማይታወቁ በአውቶ ካድ አጠቃቀም ዙሪያ ለአመራሮች እና ለሰራተኞች አቅርበው እውቀታቸውን አሸጋግረዋል፡፡  ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አድርገው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል። 

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የጽ/ቤቱ የፕሮሰስ ካውንስል አባላት የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤቱ የፕርሰስ ካውንስል አባላት በጽ/ቤቱ የሚገነቡ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ። ከጎብኝዎች ለመረዳት እንደተቻለው በበጀት አመቱ ተጀምረው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ከጊዜና ከጥራት አኳያ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችም በመልካም አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል ። በመሆኑም ጅምር ፕሮጀክቶችን ጥራታቸውን ጠበቀው ከተቀመጠው ጊዜ ባነሰ መልኩ ለማጠናቀቅ ያሉ ርብርቦች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በማሳሰብም ነው።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በጽ/ቤቱ የወርቃማው ሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ የወርቃማው ሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ። ከመርሀ ግብሩ ለመረዳት እንደተቻለው በጽ/ቤቱ የምህንድስና ግዢ ቡድን ፈጻሚ በሆኑት በኢንጂነር አሸናፊ አቅራቢነት የምህንድስና ግዢ አፈጻጸም ስርአትን በተመለከተ በተደረገው የእውቀት ሽግግር ላይ ከቡድኑ ውጪ ላሉ የጽ/ቤቱ ፈጻሚዎች በመሠረታዊነት የግዢ አፈጻጸም ስርአት ላይ ገንቢ የሆነ የእውቀት ሽግግር መደረጉን ከጽ/ቤቱ ተሳታፊዎች የተገለጸ ሲሆን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ተጠቁሟል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በክ/ከተማው ዲ/ግ/ስ/ጽ/ቤት እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀምን ጎበኙ።

የልደታ ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በክ/ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ጎበኙ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት በክ/ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየሰራን ነው ብለው ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁም የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ ከተማዋን የአፍሪካ የብልፅግ ተምሳሌት ለማድረግ እየሰራነው ላለው ስራ አጋዥ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል። ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ወደ ስራ ማስገባት የስራችን መመሪያ አድርገን እየሰራን ነው ብለዋል ወ/ሮ አበባ። የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐፍቱ ብርሀኑ እንደተናገሩት በለውጡ መንግስት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ ባህል ሆኗል ብለው የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም የ24/7 የስራ ባህልን በመጠቀም የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ በአጠረ ጊዜ በማጠናቀቅ ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ሐፍቱ አክለውም በክ/ከተማችን እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች ለትውልድ ተሻጋሪ ናቸው ብለው ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ወደ ስራ እናስገባለን በማለት ተናግረዋል። የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናርዶስ መክር በበኩላቸው ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በአጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ ባህል አድርገን እየሰራን ነው። በክ/ከተማችን የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶች ልዩ ክትትል በማድረግ በአጭር ጊዜ አጠናቀን ወደ ስራ እናስገባለን ሲሉ ገልፀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የሥራ ቦታ የማዘመንና ለሥራ ምቹ የማድረግ ሥራ በመሠራት ላይ መሆኑን ተገለጸ

የሥራ ቦታ የማዘመንና ለሥራ ምቹ የማድረግ ሥራ በመሠራት ላይ መሆኑን ተገለጸ ። በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የሥራ ቦታን የማዘመንና ለሥራ ምቹ የማድረግ ሥራ በመሠራት ላይ መሆኑንና በመሰራት ላይ ያለውም ስራ እንዳስደሰታቸው የጽ/ቤቱ አንዳንድ ፈጻሚዎች ገለጹ። በአካልም ለማየት እንደተቻለው ጽ/ቤቱ ውብና ለሥራ ምቹ መሆኑን የሚገልጹ እይታዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልምድ ልውውጥ እና የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተከናወነ።

ዛሬ በረፋዱ ከሥራ ጅማሮ አስቀድም በነበረው የልምድ ልውውጥ እና የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ላይ በኮንትራት አስተዳደር ቡድን የእውቀት አሸጋጋሪነት ተከናውኖ ውሏል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት የ9 ወራት የፅ/ቤቶች እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ።

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በ9 ወር ታቅደው የተከናወኑ የፅ/ቤቶች አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ስራዎች ላይ ተወያይቷል። በመድረኩ ላይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነ ደረሰን ጨምሮ የክ/ከተማ ሴክተር ፅ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባለፉት 9 ወራት የተሰራው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው በጋራ የመስራት ባህላችንን በማሳደግ የነዋሪዎቻችንን ጥያቄዎች ማርካት መቻል አለብን ብለዋል በተጨማሪም ተቋማት ተግባራትን በቅንጅታዊ አሰራር በመምራት በቀሪዎቹ ጥቂት ወራቶች እቅዶቻችንን በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ በ2017 በጀት አመት በ9 ወራት ታቅደው የተከናወኑ መደበኛ እና ወቅታዊ ስራዎችን የነበራቸው ውጤታማ አፈፃፀም የተሻለ እንደነበር ገልፀው ቀሪ ተግባራትን አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ አስገንዝበዋል። ባለፉት 9 ወራት በስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ለ18,709 ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን 584 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ለ 60 ኢንተርፕራዞች 51,000,000 ብር ብድር ማመቻቸትም የተቻለ ሲሆን 10,014 ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር በመፍጠር 484,000,000 ገቢ እንድያገኙ ተደርጋል፡፡ አስተዳደሩ በ9 ወር ውስጥ በልደታ ክ/ከተማ በገቢ ቅርጫፍ ፅ/ቤት 2,348,089,000 ብር 102.19 ፐርሰንት ብር ከገቢ ሰብሳቢ ተቋማት መሰብሰብ የቻለ ሲሆን የልደታ ክ/ከተማ ፈይናንስ ፅ/ቤት 1,016,000 ብር በኦዲት ተመላሽ ማድረግ መቻሉን ተገልፆል፡፡ ከዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች አንፃር በመንግስት የተሰሩ 15 ፕሮጀክቶች ክትትል በማድረግ 8 ግንባታቸውን ያጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ርክክብ ያከናወነ ሲሆን በቤቶች አስተዳደር 87,104,540 ሚሊዮን የሚጠጋ ገቢ ከኪራይ ና ከንግድ ኪራይ መሰብሰብ መቻሉን እና በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 228 የመንግስት ቤቶች በህግ በማስወሰን ለልማት ተነሺና ለደሀ ደሀ አካላት ርክክብ ተደርጋል፡፡ ጤናን በተመለከተ የመሰረታዊ መድሃኒት ስርጭት 95 በመቶ እንዲሁም የህይወት አድን መድሃኒት አቅርቦት 92 በመቶ ማድረስ የተቻለ ሲሆን በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ለ 90,008 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የማእድ ማጋራት ስራ እና የ" 571" አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እድሳት በማከናወን ከ አንድ ቢሊዬን ብር በላይ ለተለያዩ የመሰረታዊ ልማት ስራዎች በበጎ ፍቃደኞች መሰብሰብ መቻሉንም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል፡፡ ከወጣቶች እና ስፖርት ስራዎች አንፃር ለ 209,857 ወጣቶች በተለያዩ ርእሰ ጉዳዬች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ለ 10,247 ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ከፍትህ ስራዎችን በተመለከተ ባለፉት 9 ወራት 214 መዝገቦች የተንቀሳቀሱ ሲሆን በ108 መዝገቦች ውሳኔ አግኝተዋል።ውሳኔ ካገኙት 108 መዝገብ ውስጥ" 102 "ለመንግስት ተወስነዋል። ውሳኔ ካገኙት መዝገቦች 39,941,710 ብር የሚገመት የመንግስት ሀብት ማዳን ተችሏል። የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲሁም ቅሬታዎችን በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት "145" የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በክ/ከተማ እና ወረዳ መፍታት መቻሉም በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የምርት አቅርቦት ማሳደግ፣የከተማ ግብርና ስራዎችን ውጤታማ ማድረግ የሪፎርም ስራዎች፣የከተማ ፅዳት እና ማሳዋብ ስራዎች፤በማህበራዊ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰብ ያሉበት ደረጃ በልደታ ክ/ከተማ ፕላንና ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ክብረት አሳምነው ሪፖርት ቀርባል።

image
image
image
image