image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በክ/ከተማው ዲ/ግ/ስ/ጽ/ቤት እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀምን ጎበኙ።

ሚያዚያ 16, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ በክ/ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ጎበኙ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት በክ/ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየሰራን ነው ብለው ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁም የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ ከተማዋን የአፍሪካ የብልፅግ ተምሳሌት ለማድረግ እየሰራነው ላለው ስራ አጋዥ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል። ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ወደ ስራ ማስገባት የስራችን መመሪያ አድርገን እየሰራን ነው ብለዋል ወ/ሮ አበባ። የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐፍቱ ብርሀኑ እንደተናገሩት በለውጡ መንግስት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ ባህል ሆኗል ብለው የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም የ24/7 የስራ ባህልን በመጠቀም የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ በአጠረ ጊዜ በማጠናቀቅ ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ሐፍቱ አክለውም በክ/ከተማችን እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች ለትውልድ ተሻጋሪ ናቸው ብለው ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ወደ ስራ እናስገባለን በማለት ተናግረዋል። የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናርዶስ መክር በበኩላቸው ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በአጠረ ጊዜ ማጠናቀቅ ባህል አድርገን እየሰራን ነው። በክ/ከተማችን የጀመርናቸውን ፕሮጀክቶች ልዩ ክትትል በማድረግ በአጭር ጊዜ አጠናቀን ወደ ስራ እናስገባለን ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች