image
image
image
image
image

የዕለተ ሰኞ የአመራርና ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

ጥቅምት 10, 2018
የዕለተ ሰኞ የአመራርና ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ የእለተ ሰኞ ማለዳ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች መካከል የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሐ ግብረ ተካሂዷል። የዕለቱ መርሐ ግብር የተመራው በጽ/ቤቱ የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን መሪ በሆኑት በወ/ት በኮከቤ ተ/ማርያም ሲሆን ትኩረቱንም በአዎንታዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ያደረገ ሆኖ በርካታ ልምዶችና ተሞክሮዎች ተንሸራሽረውበታል፡፡ በመጨረሻም ሁሉም አመራሮች እና ሰራተኞች የእለቱን የእውቀት ሽግግር አከናውነው በተነቃቃ የሥራ መንፈስ የሳምንቱን መደበኛ ስራ ጀምረዋል።  ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች