የልደታ ክ/ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በማሳካት ረገድ ባለፉት ዓመታት በከተማዋ ስር ሰዶ የቆየውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት በመቅረፍ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ግንባታ ያካሄዳቸው እንቅስቃሴዎች ጅምር ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡
ሆኖም ግን ጽ/ቤቱ በነበረው አደረጃጀት ጥራት ያለው የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ግንባታ በማካሄድ ለከተማችን ነዋሪ በሚፈለገው ጊዜ ተደራሽ ማድረግ ያልቻለ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በሚል በአዲስ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት ውስጥ የፕሮጀክት ዝግጅት፤ ስታንዳርድ ዝግጅት፤ ክትትልና ቁጥጥር፤ የኮንትራት አስተዳደር እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት፤ ክትትልና ቀጥጥር የሚሉት በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በመሆኑም የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር የሚያከናውናቸውን የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች ዕቅድና የአገልግሎት ስታንዳርድ የያዘ የዜጎች ስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
ጽ/ቤቱ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና ለማቀላጠፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ተገልጋዮች ወደ ጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት፤ የሚወስደውን ጊዜ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸው ወጪና እንዲሁም በእነርሱ በኩል ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመላከተ የተገልጋዮች ቻርተር ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡
የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ
-
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የከተማዋን የህዝብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ለቀጣይ ሁለት የስትራተጂክ ዘመናት ሊኖር የሚችለውን የህዝብ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህንን ሊሸከም የሚችል የማህበራዊ ተቋማት ለመገንባት፤
- አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግና፣
- በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡
- በከተማዋ የሚገነቡ ግንባታዎች በጊዜ፣ በጥራትና በወጪ ቆጣቢነት ከመገንባት ባሻገር ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ደረጃውን የጠበቀ የግንባታ ግብዓት ፍተሻ ለማድርግ፤ ተቋማት ከግንባታ ፍላጎት መለየት ጀምሮ በግንባታ ሂደትና በርክክብ ወቅት የሚጠበቅባቸውን በግልጽ በማስቀመጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከመከሰታቸው በፊት በማረም ስራን ለማቀላጠፍ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች (Starategic Themes)
-
የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት፣
- የውለታ አስተዳደርና ግንባታ ርክክብ፣
- የግንበታ ግብዓት ጥናትና ጥራት ቁጥጥር፣
ስትራቴጂያዊ ውጤቶች (Strategic Results)
-
ስታንዳርዱን ጠብቆ የተዘጋጀ የግንባታ ዲዛይን፣ የስራ ተቋራጭና የአማካሪ ግዢ፤
- በተገነቡ የማህበራዊ አገልግልት መስጫ ተቋማት ኅብረተሰቡ የሚፈልገውን ግልጋሎት ተጠቃሚና ተደራሽ ይሆናል፤
- የመንግስት ተቋማት ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ያደርጋል፤
የተገልጋዮች መብት
- ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
- ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
- በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
- ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
- ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤
የተገልጋዮች ግዴታዎች
- ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
- ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
- ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት