የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራቶች
- 1. በፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
-
የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ለሚሰራላቸው ፕሮጀክቶች ፕላን ስምምነት እንዲያቀርቡ መጠየቅና ክትትል ማድረግ
- በሚመለከተው ባለድርሻ አካለት ረቂቅ የፕሮጀክት የአዋጭነት ሰነዱን ማስተቸት
- የተዘጋጀውን የመጨረሻ ዲዛይን /Final Design/ በሌሎች ባለሙያዎች እና ጥያቄ አቅራቢያው ተቋም በተገኘበት ማስገምገም
-
- 2. በምህንድስና ግዢ ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- ለአማካሪና ለስራ ተቋራጭ የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት
- የፀደቀን የጨረታ ሰነድ ለተቋራጭና አማካሪ መሸጥ
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ማብራሪያ መስጠት
- ተጫራቾች በቴክኒክና ፋይናንሻል ግምገማ ውጤት ላይ ቅሬታ ካቀረቡ ምላሽ መስጠት
-
- 3. በኮንትራት አስተዳደር ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- አማካሪ ድርጅት፣ ሰርቪየር እን የመጨረሻ ተጠቃሚ ተቋም በተገኙበት ከስራ ተቋራጩ ጋር በቼክሊስት መሰረት የሳይት ርክክብ ማድረግ
- ፕሮጀክቶች በውለታ ላይ በተቀመጠው ጥራት፣ የጊዜ ሰሌዳና የውለታ ዋጋ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን መከታተል
- የአማካሪና የስራ ተቋራጭ የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ መቀበልና ተገቢነቱን ማረጋገጥ
- የግንባታ ስራው በውሉ መሰረት በጥራት መሰራቱን በማረጋገጥ ጊዜያዊ የመረካከቢያ ሰነድ በማዘጋጀት የመጀመሪያ ርክክብ መፈጸም
- የመጀመሪያ ርክክብ ከተፈጸመ ከ1 ዓመት በኋላ ግንባታው የሚስተካከል ስራ ካለው እንዲታረም ማድረግ
- የመጨረሻ ክፍያን በውለታው መሰረት አስልቶ ማቅረብ
- ከተቋራጭ ጋር የመጨረሻ ርክክብ መፈጸም
-
- 4. የመንግስት ኮንስትራክሽን ኦዲት ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
-
ተጨማሪ የስራ ትዕዛዝ /Variation Order/ እና ሌሎች ከውለታ ሰነድና ዲዛይን /Drawing/ ላይ የሌሉ የግንባታ ስራዎች Excuted Works/ በአግባቡ መጠናቀቅቸውን የመስክ ምርመራ እና ልኬቶችን መውሰድ
- ከTake off, BOQ & Grand Summery ላይ ልዩነት የተፈጠረባቸውንና በመስክ ምልከታ የተገኙ ግኝቶች ላይ ከስራ ተቋራጩ ጋር መተማመን ላይ መድረስና የፕሮጀክቱን የመጨረሻ ክፍያ ኦዲት ሪፖርት ማተናቀቅ
-