image
image
image
image
image

የጀነራል ጃገማ ኬሎ ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ስራው ተጠናቆ የህንጻ ምርቃት ስነ ስርአት ተከናወነ።

ሀምሌ 20, 2018
የጀነራል ጃገማ ኬሎ ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ስራው ተጠናቆ የህንጻ ምርቃት ስነ ስርአት ተከናወነ። "ትኩረታችን ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ በመገንባት የከተማችንን ብልፅግና ማረጋገጥ ነው" ወ/ሮ አበባ እሸቴ በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከተገነቡ 28 የጤና ፕሮጀክቶች መካከል 22 ያህሉ በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባስተላለፍት መልዕክት ዛሬ የተመረቁ የጤና ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ ጤናማ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና አምራች ዜጋ ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ለመሆኑን ምስክር ናቸው ብለው የተመረቁት ጤና ጣቢያዎች ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆኑ የሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከተማ አስተዳደሩ ከ4 ቢሊየን በላይ ወጭ በማውጣት በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብዓትና በባለሙያዎች እንዲደራጁ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል። ዛሬ የተመረቁት የጤና ፕሮጀክቶች ለነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ናቸውም ብለዋል። ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ላደረገው ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ምስጋና አቅርበዋል። ዜናው የልደታ ክፍለ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ት ነው።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች