ዓላማ 1. የፕሮጀክት ጨረታን ማካሄድ
ስታንዳርዱን ጠብቀው የተዘጋጁና ወቅቱን ጠብቆ የጸደቁ የጨረታ ሰነድ ብዛት
-
ተግባር 1. ለ 9 ፕሮጀክቶች የግንባታ ጨረታ ሰነድ ማዘጋጅት ፣
- ተግባር 2. 9 የስራ ተቋራጭ፣ የግንባታ ክትትል እና ዲዛይን ዝግጅት አማካሪ ጨረታ ሰነድ ማዘጋጅት ፣
- ተግባር 3. የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ እንዲወጣ ለዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግዥ ቡድን መላክ ፣
- ተግባር 4. የፀደቀውን የጨረታ ሰነድ ለተጫራቾች መሸጥ
ሪፖርት ማዘጋጀትና መጠረዝ ፣
- ተግባር 5.የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ማብራሪያ መስጠት፣ ጨረታው
የሚከፈትበትን ቀንና ሰዓት ለተጫራቾች ማሳወቅ ፣
- ተግባር 6. የጨረታ ሰነድ ሽያጩ እንደተጠናቀቀ በጨረታ መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት
የሚመለከታቸው አካላት እንዲገኙ በማድረግ ጨረታው እንዲታሸግ እና እንዲከፈት ክትትል
ማድረግ፣
- ተግባር 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሲፒኦ (CPO) ለዲዛይንና ግንባታስራዎች አስተዳደርና ፋይናንስ
ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን አስፈርሞ ማስረከብ፣
- ተግባር 8. የጨረታ ቃለ ጉባኤ እና ተያያዥ ሰነዶችን በሃርድና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ መያዝ፣
- ተግባር 9. የጨረታውን ቴክኒካል ግምገማ ማከናወን፣ የቴክኒክ ግምገማውን ውጤቱንም በምህንድስና ግዥ ቡድን
ማፅደቅና ለተጫራቾች ማሳወቅ፣
- ተግባር 10. ተጫራቾች በቴክኒክ ግምገማው ውጤቱ ላይ ቅሬታ ካቀረቡ ለምህንድስና ግዥ ቀርቦ ስለስራው
ማስረዳት፣ አስፈላጊ መረጃ መስጠት፣ ችግር በታየባቸው ላይም የማስተካከል ስራ መስራት ፣
- ተግባር 11. የተስተካከለውን የቴክኒክ ግምገማ ውጤትን በምህንድስና ግዥ ቡድን አቅርቦ ማፅደቅ፣
- ተግባር 12. የፀደቀውን የቴክኒክ ግምገማ ውጤት በማስታወቂያ ቦርድ ላይ መለጠፍ እና በደብዳቤም
ለተጫራቾች ማሳወቅ ፣
- ተግባር 13. የቴክኒክ ግምገማ ውጤት ላለፉ ተጫራቾች ፋይናንሽያል የሚከፈትበትን ቀን ለተጫራቾች ማሳወቅ፣
በእለቱም ታዛቢዎች በተገኙበት ፋይናንሽያል እንዲከፈት ክትትል ማድረግ ውጤቱንም ለተጫራቾች
ማሳወቅ፣
- ተግባር 14. የጨረታውን አጠቃላይ ውጤት ለዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቅርቦ ማጽደቅ
ሲጠናቀቅ ከኮንትራት አስተዳደር ቡድን ጋር በጋራ ከስራ ተቋራጩ ርክክብ መፈፀም ፣
- ተግባር 15. አጠቃላይ የጨረታ ሂደቱ ከተጠናቀቀ እና ውጤት ለዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ቀርቦ
ከፀደቀ በኋላ ለአሸናፊዎች ማሳወቅ፣
ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው የተዘጋጁ የውለታ ሰነድ ብዛት
-
ተግባር 1. የ9 የግንባታ ክትትል አማካሪና የ9 የስራ ተቋራጭ የውለታ ሰነድ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት
ማዘጋጀት ፣
- ተግባር 2. በተዘጋጀው የውለታ ሰነድ በእማኝ ቦታ ላይ በመፈረም፣ ለዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
ውል ላይ አስፈርሞ አሸናፊ ተጫራቾችን በማስፈረም ለኮንትራት አስተዳደር ቡድን መላክ፣
- ተግባር 3. የጨረታ አሸናፊዎችን የጨረታ ሰነዶች አደራጅቶ በሃርድና ሶፍት ኮፒ መያዝ፣